AroundMaps Logo
Search
Add Listing

ኦርቶዶክስ ቱብ - Orthodox Tube

0

About ኦርቶዶክስ ቱብ - Orthodox Tube

"ለሚጠይቁዋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ"
1ኛጴጥ 3:15

Tags

Map

Item Reviews - 4

Anynomous

"

❖የክርስትና ስም ለምን ያስፈልጋል?❖ ጥቂት የማንባል ሰዎች ከነ መሰየሙም የክርስትና ስማችንንም የማናስታውስ ልንኖር እንችላለን፡፡ የክርስትና ስም አንድ የሚጠመቅ ሰው በሚያጠምቀው ካህን የሚሰጠው ወይም የሚጸድቅለት ስያሜ ነው፡፡ ይህንን ስም ቤ/ክ ዝም ብላ ለህጻናቱ የምትለጥፍ የሚመስላቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ በጥምቀት ግዜ ቤ/ክን ልጆቿን ስትቀበል እንዲሁ አይደለም ተገቢ ስም አውጥታ ከመንፈስ ቅዱስ በጥምቀት ዳግመኛ ወልዳ ቅበዐ ሜሮን ቀብታ የሚንከባከብ የክርስትና አባት እናት ሰይማ በመስቀሉ ቃል አስገብታ ቅዱስ ስጋና ደሙን መግባ ነው፡፡ የክርስትና ስም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እና ክርስቲያናዊ ትውፊት አለው፡፡... ብዙ ነብያት እና ቅዱሳን ካላቸው መጠሪያ ሰም በተጨማሪ እራሱ አምላካችን አዳዲስ ስም ሲያወጣላቸው እናያለን ለምሳሌ፡- አብራምን ☞ አብርሃም ያይቆብን ☞ እስራኤል ስምዖንንን ☞ ጴጥሮስ ሳኦልን ☞ ጳውሎስ እያለ ሲጠራቸው ለምን በአዲስ ስም መጥራት እንደፈለገ አንዳች ነገር ልንገነዘብ ይገባል፡፡ ✞ ዓላማውስ ምንድን ነው? 1.ቋሚ የቅዱሳን መታሰቢያ እንዲሆን፡- በት.ኢሳ 56:5 አምላክ ለቅዱሳን የማይጠፋ ስም እና የዘለዓለም መታሰቢያ እንደሰጣቸው እናነባለን፡፡ስለዚህ በተለያዩ ቅዱሳን ላይ የነበረውን ፀጋ እና በረከት ለመካፈልና እንዲሁም እንደነሱ የበረታን እንድንሆን በስማቸው እንሰየማለን የጌታችንንም ስሙን ዘርፍ በማድረግ እንዲሁ እንጠቀምበታለን፡፡ 2.ለተጠማቂውም በረከት እንዲሆንለት፡- በምሳ 10:6 የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው ይላል፡፡ ስለዚህ በስማቸው በመሰየም ከላይ እንደገለጽነው መታሰቢያቸውን እና በረከታቸውን ለመካፈል ሲረዳን ይህን ጸጋ ለማግኘት በቅዱሳን ስም በመሰየም የክርስትና ስም ይወጣልናል፡፡ 3.መጠሪያ ስም ነው፡- በቀድሞው ስርአት የክርስትና ስም ለሁልጊዜውም መጠሪያ ነበር፡፡ ከግራኝ መሐመድ መነሳት አስቀድሞ የነበሩ ምዕመናን በክርስትና ስማቸው ነበር የሚጠሩት፡፡ነገር ግን መከራው ሲበዛባቸው ከርስታቸው ላለመሰደድ ሲሉ ተለዋጭ ስም በማውጣት መጠቀም ጀመሩ ከዛን ግዜ ጀምሮ ይህ ነገር እየተስፋፋ መጥቶ ከነ ጭራሹ ለመለወጥ በቃ፡፡ ☞ የማይገባ የክርስትና ስም በአምላክ ስም በቀጥታ መጠራት አይገባም ለምሳሌ፡- አማኑኤል፣ኤልሻዳይ፣ኢየሱስ እነዚህ ስሞች ለሠው ልጆች መጠናችን ስላልሆኑ መጠቀም የለብንም፡፡ በዚህ ምትክ ገብረ አምላክ፣ሣህለ ሥላሴ፣ፍቅርተ ክርስቶስ ፣ዘአማኑኤል በማለት መሰየም ይቻላል፡፡ ☞በቅዱሳንም ስም በቀጥታም ሆነ ዘርፍ እየተደረለት መሰየም ይቻላል፡፡ ለምሳሌ፡- ዘማርያም፣ዘሚካኤል፣አጸደ ማርያም፣ ተክለ ሐይማኖት ወዘተ... ስለዚህ ስርአቱን በመጠቀም ከሚገኘው በረከት ተሳታፊዎች እንድንሆን አምላክ ይርዳን፡፡

Like and share

See More "

26 June 2023

Anynomous

"

ከግሸን ንግስ መልስ ወደገደል ተንደርድረው በእመቤታችን በድንግል ማርያም ድንቅ ተዓምራት አንድም ሰው ሳይጎዳ የተረፉት ሁለት ቅጥቅጥ አይሱዙ መኪናዎች ፡፡ ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን፡፡

"

03 October 2023

Anynomous

"

"የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።" (መዝሙረ ዳዊት 34:7፤) i.e (የእግዚአብሔር መልአክ ያድናል)

"

27 August 2023

Anynomous

"

" አቤቱ እስከ መቼ ዝም ትላለህ?" ሁሉም ሰው ሊያዳምጠው የሚገባ ወቅቱን የጠበቀ ልብ የሚነካ ስብከተ ወንጌል በዲ/ን ዳንኤል ክብረት -አቤቱ እስከ መቼ ዝም ትላለህ? -እስከ መቼ ነው በአባቶቻችን ምክንያት እየተፈትን የምንቀጥለው? - የምናከብረው እንጂ የማንፈተንበት አገልጋይ መቼ ነው ምናገኘው? - እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሉ ቀሳውስት መቼ ነው የምናገኘው? -እንደነ ቅዱስ እስጢፋኖስ የመሰሉ ዲያቆናት መቼ ነው የምናገኘው? -እንደነ ቅዱስ ጳውሎስ ያሉ መናንያን አገልጋይዎች መቼ ነው የምናገኘው? ... - እንደነ አባ እንጦንስ አባ መቃርስ ያሉ መነኮሳት መቼ ነው የምናገኘው? - እንደነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ያሉ ባሕታውያን መቼ ነው የምናገኘው? -እንደዚህ ዓይነት ሰው የማታነሳው እስከ መቼ ነው?

See More "

31 July 2023

Add Reviews & Rate item

Your rating for this listing :

Help Us to Improve :

Location / Contacts :

Nearby Places :