AroundMaps Logo
Search
Add Listing

About Haramaya University Students Union - HUSU

we are here to inform you

Tags

Description

THIS IS WHERE STUDENTS PRESENT THEIR CLASMATES

Map

Item Reviews - 4

Anynomous

"

የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን ተማሪዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች ለተፈናቃዮች የ143ሺህ 617 ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡ via Amhara Mass Media Agency ባሕር ዳር፡ሰኔ 09/2010 ዓ/ም(አብመድ)የሐሮማያ ዩኒቨርስቲ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ፡፡ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተገኝተው የ143ሺህ 617 ብር ለኮሚቴዎች አስረክበዋል ፡፡ በዶክተር አበበ አስቻለው እና በተማሪ ያስከብራል ወዳጄ በኩል ነው ገንዘቡ በአካል የተሰጣቸው፡፡በቀጣይ መንግስት ዜጎቹ በዘላቂነት የሚቋቋሙበትን እና መፍትሄ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል፡፡... ተፈናቃዮቹም ለተደረገላቸው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል:: ዘጋቢ፡-አይሸሽም አባተ

See More "

15 June 2023

Anynomous

"

ሰበር ዜና ክፍት የነበረውን የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ኃላፊ ለመመረጥ የተደረገውን ውድድር መሰረት በማድረግ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር ቦርድ ከግንቦት 21 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮፌሰር ጄይላን ወልዬ ሁሴንን የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች ጉዳይ ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ ሾሟል። በዚሁ መሰረት ፕሮፌሰር ጄይላን ወልዬ ዛሬ በአዲሱ ቢሮአቸው ተገኝተው ስራቸውን ጀምረዋል፡፡

"

30 May 2023

Anynomous

"

Part 1 ታዋቂው ደራሲና የአዕምሮ ሃኪም ዶ/ር ምህረት ደበበ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ያቀረበዉ Inspirational Speech By TemariTube.Net

"

21 May 2023

Anynomous

"

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲን ላለፉት ሶስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት የመሩት ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ ከዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በፈቃዳቸው ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡

ፕሮፌሰር ጨመዳ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ የሰሩ ሲሆን ላለፉት ስድስት ዓመታት በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትነትና በፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ ለዩኒቨርሲቲው የሴኔትና የአስተዳደር ካውንስል አባላት እንደገለፁት ባለፉት ሶስት ዓመታት የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካት ባላቸው አቅም በሙሉ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርና በርካታ ለውጦች ማስመዝገብ መቻላቸውን ጠቁመው ለተገኙት ውጤቶች መሳካትም አብረዋቸው ሲሰሩ የነበሩ አካላትን በሙሉ አመስግነዋል፡፡

...

በየጊዜው እየተማርን መስራትና መለወጥ አለብን በሚል መርህ ዩኒቨርሲቲውን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበር ፕሮፌሰር ጨመዳ ጠቁመው አዲስ የሚመጣው ፕሬዝዳንትም የተጀመሩ ስራዎችን ከግብ የሚያደርስ በመሆኑ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙሉ ለእሳቸው ያደረገውን የስራ ድጋፍ ለአዲሱም ፕሬዝዳንት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለረጅም ዓመታት በመምህርነት ፣ በተመራማሪነት እንዲሁም በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ላይ በማገልገል ላይ ያለሁት ዩኒቨርሲቲውን ከልቤ ስለምወደውና ቤቴም ስለሆነ ፈልጌና መርጬው በመሆኑ ከኃላፊነት ብለቅም በማስተማርና በምርምር ስራዬ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ እቀጥላለሁ ሲሉ ፕሮፌሰር ጨመዳ ተናግረዋል፡፡

ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንትነታቸው እንዲነሱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያስገቡት መልቀቂያ ተቀባይነት በማግኘቱ ከዛሬ ግንቦት 9 ቀን 2010 ጀምሮ ከኃላፊነታቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ ከሀምሌ ወር 2007 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 18/2008 ዓ.ም በተጠባባቂ ፕሬዝዳንትነት ፣ ከጥቅምት 19/2008 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በፕሬዝዳንትነት ያገለገሉ ሲሆን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲም 6ኛው ፕሬዝዳንት ነበሩ፡፡

ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ የለቀቁትን የፕሬዝዳንትነት ቦታ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የአመራር መረጣና ምደባ መመሪያ መሰረት ምርጫው እስኪደረግ የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል ዩሱፍ በተወካይነት ዩኒቨርሲቲውን እንዲመሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ውክልና ተሰጥቷቸዋል፡፡

See More "

17 May 2023

Add Reviews & Rate item

Your rating for this listing :

Help Us to Improve :